Watch ሱረቱል አል ፈጅር - ምርጥ ቁርዓን አቀራር በቃሪ ሃኒ አረፊኢ in New Channel | Channify

c-TYptRXcsf3jy9OCZ 4795076 sTywaiRAIrk
Views 253,662
Likes 1,472
Comments 560
Published Feb 25, 2016
Channel ኢስላማዊ እውቀቶች - Islamic Knowledge

Add More Videos To your Channel

አል-ፈጅር (የጎህ ምዕራፍ) 89:1 በጎህ እምላለሁ። By the dawn 89:2 በዐሥር ሌሊቶችም። And [by] ten nights 89:3 በጥንዱም በነጠላዉም። And [by] the even [number] and the odd 89:4 በሌሊቱም በሚኼድ ጊዜ። And [by] the night when it passes, 89:5 በዚህ (መሐላ) ለባለ አእምሮ ታላቅ መሐላ አለበትን? Is there [not] in [all] that an oath [sufficient] for one of perception? 89:6 ጌታህ በዓድ እንዴት እንደ ሠራ አታዉቅምን? Have you not considered how your Lord dealt with 'Aad - 89:7 በኢረም፣ በባለ ረዣዢሚቱ አዕማድ፤ [With] Iram - who had lofty pillars 89:8 በዚያች ብጤዋ በአገሮች ዉስጥ ያልተፈጠረ በሆነችዉ፤ The likes of whom had never been created in the land? 89:9 በሰሙድም፣ በእነዚያ በሸለቆዉ ቋጥኝን የቆረጡ በሆኑት።፤ And [with] Thamud, who carved out the rocks in the valley? 89:10 በፈርዖንም ባለ ችካሎች በሆነዉ፣ And [with] Pharaoh, owner of the stakes? - 89:11 በእነዚያ በአገሮች ላይ ግፍ የሠሩ፣ [All of] whom oppressed within the lands 89:12 በዕርሷም ዉስጥ ጥፋትን ያበዙ በሆኑት (እንዴት እንደሠራ አታዉቅምን?) And increased therein the corruption. 89:13 በእነርሱ ላይም ጌታህ የቅጣትን አለንጋ አወረደባቸዉ። So your Lord poured upon them a scourge of punishment. 89:14 ጌታህ በመጠባበቂያ ላይ ነዉና። Indeed, your Lord is in observation. 89:15 ሰዉማ፣ ጌታዉ በሞከረዉ ጊዜ፣ ባከበረዉና ባጣቀመዉም (ጊዜ) ጌታዬ አከበረኝ (አበለጠኝ) ይላል። And as for man, when his Lord tries him and [thus] is generous to him and favors him, he says, "My Lord has honored me." 89:16 በሞከረዉና በእርሱ ላይ ሲሳዩን ባጠበበ ጊዜማ ጌታዬ አሳነሰኝ ይላል። But when He tries him and restricts his provision, he says, "My Lord has humiliated me." 89:17 ይከልከል፤ ይልቁንም የቲምን አታከብሩም፤ No! But you do not honor the orphan 89:18 ድኻንም በማብላት ላይ አትታዘዙም፤ And you do not encourage one another to feed the poor. 89:19 የዉርስንም ገንዘብ የመሰብሰብን አበላል ትበላላችሁ፤ And you consume inheritance, devouring [it] altogether, 89:20 ገንዘብንም ብዙን መዉደድ ትወዳላችሁ። And you love wealth with immense love 89:21 ተዉ፤ ምድር ደጋግማ በተሰባበረች ጊዜ፤ No! When the earth has been leveled - pounded and crushed - 89:22 መላእክትም ሰልፍ ሰልፍ ሆነው ጌታህ፣ (ትዕዛዙ) በመጣ ጊዜ፤ And your Lord has come and the angels, rank upon rank, 89:23 ገሀነምም በዚያ ቀን በተመጣች ጊዜ፣ በዚያ ቀን ሰዉ (ጥፋቱን) ይገነዘባል። መገንዘቡም ለርሱ ከየቱ? And brought [within view], that Day, is Hell - that Day, man will remember, but what good to him will be the remembrance? 89:24 ዋ እኔ! ምነዉ በሕይወቴ (መልካምን ሥራ) ባስቀደምኩ ኖሮ ይላል። He will say, "Oh, I wish I had sent ahead [some good] for my life." 89:25 በዚያ ቀንም የርሱን አቀጣጥ አንድም አይቀጣም። So on that Day, none will punish [as severely] as His punishment, 89:26 የእርሱንም አስተሳሰር አንድም አያስርም፤ And none will bind [as severely] as His binding [of the evildoers]. 89:27 (ለአመነች ነፍስም) አንቺ የረካሺዉ ነፍስ ሆይ! [To the righteous it will be said], "O reassured soul, 89:28 ወዳጅ ተወዳጅ ሆነሽ ወደ ጌታሽ ተመለሺ። Return to your Lord, well-pleased and pleasing [to Him], 89:29 በባሮቼም ዉስጥ ግቢ፣ And enter among My [righteous] servants 89:30 ገነቴንም ግቢ፤ (ትባላለች)። And enter My Paradise."